876просмотров
48.9%от подписчиков
11 марта 2026 г.
stats📷 ФотоScore: 964
ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ 10 ተጠቃሚዎች ወሳኝ የደህንነት ማሻሻያ ለቀቀ ማይክሮሶፍት የዊንዶውስ 10 ተጠቃሚዎች ኮምፒውተራቸውን ከጥቃት እንዲከላከሉ የሚያስችል "KB5078885" የተሰኘ አዲስ የደህንነት ማሻሻያ ይፋ አድርጓል። ምንም እንኳን ለዊንዶውስ 10 የሚደረገው መደበኛ ድጋፍ ቢቋረጥም፣ ማይክሮሶፍት ክፍያ ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ተቋማት እስከ ጥቅምት 2028 ድረስ የሚቆይ "Extended Security Update (ESU)" የተሰኘ ልዩ የድጋፍ ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ይታወቃል። ይህ አሰራር ተቋማት ወደ ዊንዶውስ 11 ለመሸጋገር ተጨማሪ ጊዜ እንዲያገኙ ታሳቢ ያደረገ የሽግግር ጊዜ ነዉ። ይህ የቀረበዉ አዲስ ዝመና በዋናነት በኮምፒውተራችን ላይ የተገኙ 79 የደህንነት ክፍተቶችን ለመድፈን የወጣ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ አስቀድሞ በጠላፊዎች እጅ ገብተው ጥቃት እያደረሱ የነበሩ አደገኛ ስጋቶች ናቸው። በመሆኑም ይህንን ማሻሻያ መጫን የኮምፒውተራችንን ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ማይክሮሶፍት አሳዉቋል። ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
876
просмотров
645
символов
Нет
эмодзи
Да
медиа

Другие посты @Success_Tech_News1

Все посты канала →
ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ 10 ተጠቃሚዎች ወሳኝ የደህንነት ማሻሻያ ለቀቀ ማይክሮሶፍት የዊንዶውስ — @Success_Tech_News1 | PostSniper